መስጊድ እና በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው ሚና
በባልታዛር እና አብደናጎ
ክፍል አምስት
በምዕራቡ ዓለም ያሉ መስጊዶች ሚና
በምዕራቡ ዓለም ያሉ መስጊዶች ተግባር ከውጪ ሲታይ በእስልምናው ዓለም ካለው ጋር የሚመሳሰል ይመስላል። ሆኖም፣ ይህ እውን የሚሆነው በተወሰነ ደረጃ ብቻ ነው። በምዕራቡ ዓለም ያሉ መስጊዶች የሚጫወቱት ሚና በአረብ እና በእስላማዊው ዓለም ካለው በእጅጉ የጠነከረ ነው
እስልምና እንደ ብሔራዊ ሃይማኖት በሚታወቅበትና ሸሪዓ የሁሉም ሕጎች እና ምንጭ በሆነበት እንዲሁም ጠቃሚ ሆነው የሚገኙ የፖለቲካ ወንበሮች በሙስሊሞች ብቻ በተያዙበት በእስላማዊው ዓለም ውስጥ መስጊዶች የሚገኙት በእስልምና ቤት ውስጥ ነው።
በዚያ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች እንደ ዲህሚ ሲቆጠሩ፤ ከሙስሊሞች ጋር የእኩልነት መብት የሌላቸውና ማንኛውም መብታቸው ከሙስሊሞች በብዙ መልኩ ያነሰ ነው። ሆኖም (መስጊዶች) በምዕራቡ ዓለም ውስጥ ሲገነቡ በጦርነት ቤት ውስጥ ስለሚገኙና ሃይማኖታቸው ሌሎችን ደምስሶ የመግዛት መብት ስለማያገኝና ግላዊ ጉዳይ ስለሚሆን እንደ ጦርነት መንደርደሪያ ቦታ በመሆን ያገለግላሉ።
መስጊድና የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ውስጥ ውስጡን በማንነት ችግር፣ ከእስልምና ፅንሰ-ሀሳብ አንፃር ከሚታዩ ማኅበራዊ-ፖለቲካዊ ነፃነቶች፣ ከውስጥ መከፋፈል የተነሳ ከሚከሰት መለያየት፣ ሙስሊም ባልሆነ አካባቢ ድምፅን ከፍ አድርጎ ከማሰማት ኃላፊነት እንዲሁም ከሚኖሩበት ኅብረተሰብ መካከል ወደ እስልምና የመጡ ሰዎችን ማጠንከርን እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ ይቸገራሉ። ስለዚህም፣ ነባራዊ ሁኔታዎቹን እንደሚከተለው እንመልከት።
1. ማንነት
ሙስሊሞች በእስላማዊ ግዛቶች ውስጥ በሚኖሩ ጊዜ በቁጥራቸው ስለሚያይሉ ምንም ዓይነት የማንነት ጥያቄ አይገጥማቸውም። ነገር ግን በምዕራቡ ዓለም በሚሆኑበት ጊዜ በተለይ ሙስሊሞች በትምህርተ ስርዓቱ ላይ የሚገጥማቸውን ጉዳይ፣ የአለባበስ ሁኔታ እንዲሁም በመካከሉ የሚገኙበት ማኅበረሰብ በልጆቻቸው እና በእነርሱ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ከመፍራት የተነሳ ከፍተኛ መረበሽ ይገጥማቸዋል።
እስልምና ሁሉም ሰዎች እኩል እንደ ሆኑ ስለማያምንና በሸሪዓ ፍርድ ቤትም ሙስሊም ወንድ እና ሙስሊም ሴት ወይም ሙስሊም የሆነና ያልሆነ እኩል ስለማይዳኙ በምዕራቡ ዓለም ውስጥ ካለውና ሰው ሁሉ በሕግ ፊት እኩልነትን የማግኘት መብት የተነሳም ይቸገራሉ።
ከሁሉም በላይ እስልምና በሃይማኖታዊነቱም በፖለቲካዊነቱም የበላይ እንደሆነ ስለሚታመንና በሃይማኖት ነፃነት ፅንሰ-ሀሳብ የማያምን መሆኑ ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ጋር የተቆራኘ ስለሆነ በምዕራቡ ዓለም ባለው ነፃነት ይቸገራሉ፡፡
2. ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ነፃነት
የግዴታ ጋብቻዎችን፣ ከአንድ ሚስት በላይ ማግባትን፣ የሴት ልጅ ግርዛትን፣ ለልጆች ተቆራጭ መስጠትን፣ ፍቺን፣ ልጅ የማሳደግ መብትን እና የመሳሰሉትን የግለሰብ እና ቤተሰብ ሕጎች በተመለከተ ግጭቶች ይነሳሉ። ከሌላ ሃይማኖት ተከታይ ወይም ሌላ ዜግነት ካላት ሚስት ጋር ተጋብተው ፍቺ በገጠማቸው ጊዜ ሙስሊም አባት ልጆቹን የማሳደግ መብት ወዲያውኑ ላያገኝ ይችላል፡፡ ለሚስቲቱ ተቆራጭ ማድረግን ደግሞ ለወንዶች የሚያደላው ሸሪዓ የማይፈቅደው ጉዳይ ሆኖ ይገኛል።
3. መከፋፈል
መከፋፈል በጎሳዎች እንዲሁም በእምነት ዓይነቶች መካከል ይከሰታል። የእስልምና ውስጥ የሚከሰተው መከፋፈል ሙስሊሞቹ የሚመጡት ከሁሉም ዓይነት የእስልምና ትምህርት ቤቶች፤ ሱኒዎች፣ ሺዓዎች፣ አሕመዲያዎች፣ ቃድያዎች፣ ዋብዮች፣ ሳላፊዎች፣ ቁራኒዮች፣ ሱፊዎች እንዲሁም ሌሎች ትምህርት ቤቶች በመሆኑ ነው። ለምሳሌ አንስተን ብንመለከት ሺዓ እራሱ እንደገና ለአምስት፣ ለሰባት፣ ለአስራ ሁለት፣ ለእስማኤሊ፣ ኮጃ፣ ቡሀራና ወደ መሳሰሉት ይከፈላል።
በሱፊዎች ውስጥም ብዙ ታሪካዎች ወይም መዋቅሮች፣ ቅርንጫፎች፣ ዘዴዎች እና አካሄዶች አሏቸው።
የጎሳ መከፋፈልም በእንግድነት በሚኖሩበት ማኅበረሰብ መካከልና ከአካባቢው ለውጥ ጋር የሚገጥማቸው ችግር ነው። በዚያ የሚገጥማቸው ችግር እርስ በእርስ በመስማማት መጓዝ፣ ወደ እስልምና ሃይማኖታቸውን የሚቀይሩ ሰዎች ማፍራት እንዲሁም ውሳኔ የማሳለፍ ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች የእስልምናን አጀንዳ እንዲገነዘቡ የማድረግ ይሆናል። እስልምና በሚኖሩበት ማኅበረሰብ መካከል ተቀባይነት እንዲያገኝ ማድረግ ዋነኛው ፈተናቸው ነው።
4. አጠቃላይ አገዛዝ
በክሁራም ሙራድ በተጻፈው ዘ ኢስላሚክ ሙቭመንት ኢን ዘ ዌስት ውስጥ እንደተገለፀው በእንግድነት የሚኖሩበትን ማኅበረሰብ ሙሉ በሙሉ በእነርሱ ቁጥጥር ስር ለማድረግ በቀጣይነት መታገላቸው አይቀሬ ነው።
የእስልምና ተከታይ ያልሆኑ ሰዎች ወደ መስጊድ ለመግባት መከተል ያለባቸው ደንቦች
በ28ኛው ረመዳን ከሂጅራ በኋላ በ1423 (ማርች 15፣ 2002) በወጣው ፋትዋ ቁጥር 26104፦
የውይይት አጀንዳ፦ በኒው ዚላንድ ሃይማኖት እና የጎሳ ጥናት የስርዓተ-ትምህርቱ አካል ናቸው። ከዚህ የተነሳ ትምህርት ቤቶቹ በየዓመቱ በአያሌ አብያተ ክርስቲያናት፣ የቡድሀዎች ቤተ መቅደስ፣ እንዲሁም በመስጊዶች ጉብኝት እንዲደረግ ያቅዳሉ። ምንም ያህል ስለ እስልምና በዝርዝር ልናስረዳቸው፣ ስለ መንፃት፣ ስለ ፀሎት እና ስለ አላህ አንድ አምላክ መሆን ልንገልፅላቸው ብንሞክርም፣ ወንዶች እና ሴቶች በአንድ ላይ መምጣታቸውን እና አንዳንዶች እንደሚሉት ሴቶቹ የወር አበባ በሚያዩበት ጊዜ ወደ መስጊድ ሊገቡ እንደሚችሉ በማሰብ ወደ መስጊድ እንዲገቡ ልንፈቅድ ይገባልን?
ፋትዋ፦ አላህን እናመሰግናለን፤ ፀሎት እና በረከት በአላህ መልዕክተኛ እና በአጋሮቹ ላይ ይሁን። የማያምኑ ሰዎች የመግባት ዕድል የማግኘታቸውን ወይም ወደ መስጊድ መግባታቸውን ጉዳይ በተመለከተ ከታች እንደተዘረዘረው ምሁራኑ በአራት ተከፍለዋል። ሆኖም ወደተቀደሰው የመካ መስጊድ መግባት እንደማይፈቀድላቸውና ያንን ቅዱስ ስፍራ መርገጥ እንደሌለባቸው በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል።
1) ካርታቢ በግልጽ እንዳስቀመጠው እንዲሁም፣ ኦማር ቢን አብደል አዚዝ ተናግሮታል ብሎ አሕመድ ማርዳዊ እንደጻፈው በየትኛውም የመስጊድ ክፍል ውስጥ ከመግባት መታገድ አለባቸው። በቁርአን 24.36 የቃፊሮች መግቢያ የአላሕ ምስጋና ከሚወሳበት ጋር ተቃራኒ ነው ተብሎ ተጽፏል።
2) የሻፊ ትምህርት ቤት ደግሞ በአረብ ሀገር ካሉ ቅዱስ መስጊዶች በስተቀረ ወደ ሌሎቹ ቢገቡ ምንም እንዳይደለ ያምናል።
3) የማሊኪ ትምህርት ቤት ደግሞ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ወደ የትኛውም መስጊድ ከመግባት መከልከል እንዳለባቸው ይናገራል።
4) በዚያ የሚገኙ ሙስሊሞች እንዲገቡ እስከፈቀዱላቸው ድረስ ወደ መስጊድ ሊገቡ ይችላሉ።
5) ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ አዎንታዊ ተፅዕኖን የሚያመጣና ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ ሙስሊም ያልሆነ ሰው ወደ መስጊድ እንዲገባ ሊፈቀድለት ይችላል።
የጳጳሱ ኡማያድ መስጊድን መጎብኘት
ፋትዋ ቁጥር 82፡50፣ በ28ኛው ሳፋር በ1422 ከሂጅራ በኋላ (ማርች 25፣ 2001)
የውይይት አጀንዳ፦ ጳጳሱ ወደ ኡማያድ መስጊድ ሊፀልዩ መግባት ይችላሉን? እንዲያውስ መግባት ይፈቀድላቸዋልን?
ፋትዋ፦ ለአላሕ ምስጋና፣ ለመልዕክተኛው ለመሐመድ እና ለአጋሮቹ ደግሞ ፀሎት እና ሰላም ይሁን። ቃፊሮችን በተመለከተና ወደ መስጊድ ለመግባት የሚያገኙትን ፈቃድ በፋትዋ 4041 በኡለማው መካከል ያለውን የአስተሳሰብ ልዩነት በገለፅንበት ወቅት አስፍረነዋል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ወይም እንደ ካፊሮች ወደ እስልምና መምጣት ዓይነት ለእስልምና ጥቅም የሚያስገኝ ጉዳይ እስከ ተፈጠረ ድረስ ካፊሮች ከተቀደሰው መስጊድ በስተቀረ ወደ ሌሎቹ መግባት እንደሚችሉ ደምድመናል። ነገር ግን የባለመስቀል ከሀዲዎች አለቃ የሆነውና ድኃና ችግረኛ ሙስሊሞችን ወደ መቅበዝበዝና ክርስትና እየመራ፣ ለመመገብ፣ ለመጠጣት እና መድኃኒት ለማግኘት ያላቸውን ፍላጎት እየጠመዘዘ የሚቀይር አለቃቸው ግን ወደ መስጊድ እንዲገባ እንፈቅድለታለን ማለት አይደለም።
በዓለም ዙሪያ ያሉትን ሙስሊሞች የሚዋጉ ክርስቲያኖች አለቃ ሆኖ ሳለ እንዴት ነው ወደ መስጊዳችን እንዲገባ የምንፈቅድለት? እርሱ ወደ መስጊድ በመግባቱ የምናገኘው አንዳችም ጥቅም የለም።
እርሱን ማስተናገዳችን እርሱን ሙስሊም እንዲሆን ለመጋበዝ አይደለም፣ ስለዚህ የእርሱ መምጣት የሚያስከትለው አንዳችም ጥቅም የለም።
የከሀዲ ወደ መስጊድ መግባት እስልምናን ማጣጣል ነው . . . ይህንን ነገር ለማቃናት መሞከርም ሌላ ዓይነት ቀለም ነው . . .
ነገር ግን፣ መቻቻልን በማስመሰል ወደ መስጊድ መምጣቱና አላሕ ከሦስት አንዱ ነው እያለ አንድ አምላክ ስለ መሆን በተለየ መልኩ የሚያቀርብን መልዕክት መሸከሙ እንግዳ ቀለም ነው።
ከመካከላቸው አንዳንዶቹ የሦስቱ ሃይማኖቶች ተከታዮች እንደ በእግዚአብሔር፣ የመጨረሻው ቀን፣ ትንቢት እና መጽሐፉ ስለሚያምኑ መሠረታዊ መነሻ እንዳላቸው የሚናገሩ ሲሆን እግዚአብሔር እንደሌለ በሚከራከሩና በሃይማኖት የለሽ ሰዎች ፊት ሲቀርቡ ክርስቲያኖች እና አይሁዳውያን ያሉበትን ኑፋቄ ረስተው በአንድነት ይቆማሉ። ከዚህም የተነሳ ካፊር የኑፋቄ ተምሳሌቱን አንድ መሆኑ ሊታወጅበት በሚገባ በአላሕ ቤት ውስጥ አፅንዖት ሰጥቶ እንዲናገር እና እንዲለማመድ አንፈቅድለትም።
መስጊዶች የእስልምና ተከታይ ባልሆኑ ሰዎች የሚደገፉበት ሁኔታ
ፋትዋ ቁጥር 6261፣ በ16ኛው ሳፋር በ1420 (አፕሪል 17፣ 1999)
የውይይቱ አጀንዳ፦ በፈረንሳይ ሊሠራ የታቀደውን መስጊድ አምላክ እንደሌለ የሚያምኑ ሰዎች በገንዘብ ለመደገፍ እና በህንፃ ግንባታው ለመሳተፍ መጠየቃቸውን በተመለከተ ሸሪዓ ምን ይላል? ሙስሊሞች ያለ ውጪ ሰዎች እርዳታ ይህንን ማድረግ መቻላቸውን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል።
ፋትዋ፦ ለአላሕ ምስጋና፣ ለአላሕ መልዕክተኛና ለአጋሮቹ ደግሞ ፀሎት እና ሰላም ይሁን። ካፊሮቹ መስጊዱን ለመገንባት ከሙስሊሞቹ ጋር ለመተባበር የተነሱበት ምክንያት ከሚከተሉት ከሦስቱ አያልፍም፦
1) በጥምረት በመሥራትና ኃላፊነትን በመጋራት ካፊሮቹ በመስጊድ እና በአስተዳደሩ ውስጥ የእኛም እጅ አለበት ለማለት ይመቻቸው ዘንድ ይሆናል። እዚያው ባለማመናቸው ውስጥ ሆነው ሳለ በሙስሊሞች ሃይማኖት እና በአምልኳቸው ውስጥ ገብተው መጣመራቸው የማይፈቀድ እና የተከለከለ ነው፤ ምክንያቱም ይህ ሁኔታ ከተፈቀደ ካፊሮቹ ሙስሊሞችን እየገዟቸው ነው ማለት ነው።
2) የሚሰጡት የሙያ እገዛ፣ ንድፉን ማዘጋጀት ወይም የመሳሰለው ሊሆን ይችላል። ካፊሮች ጠላቶቻችን ስለሆኑ በሙስሊሙ ማኅበረሰብ መካከል ይህንን ማድረግ የሚችል ሙያተኛ እስካልጠፋ ድረስ ሊተባበሩን አይገባም። ስለዚህ የሚሠሩት ሥራ አመኔታ አይጣልበትም። የመገንባቱን ሀላፊነት የወሰዱ እንደሆነ ሙስሊሞችን የሚያስከፋውን ወይም ጉዳት የሚያስከትለውን ቦታ ሊደብቁት ይችላሉ። ነገር ግን ከእነርሱ ጋር መሥራቱን የፈቀድነው አማራጭ ስላጣን ከሆነ ወይም አስቀድሞ የእነርሱ ቤተ ክርስቲያን የነበረ ወይም የሕዝብ ህንፃ ሆኖ ሙስሊሞች ከገዙት ደግሞ በውስጡ የሚደረገው የሙስሊሞች ፀሎት ተቀባይነትን ያገኛል።
3) ሌላ ምንም ጓዝ ሳይኖረው ሙስሊሞች መስጊዳቸውን እንዲገነቡ የገንዘብ እርዳታን የሚሰጡ ከሆነ ምንም ተቃውሞ አይኖርም። ምክንያቱም ነብያችን ከሮማ ገዢ ቄሳር፣ ከአንኩስ እና ከመሳሰሉት ካፊሮች ስጦታን ተቀብሏል። ተገቢ ሆኖ ከተገኘና ሙስሊሞችን የሚጠቅም እስከሆነ ድረስ ሙስሊሞች እንዲህ ያለ ስጦታን ከካፊሮች ተቀብለው ሊጠቀሙበት ወይም በመስጊድ ውስጥ ሊያኖሩት ይችላሉ።
እስላማዊ ያልሆነ ፀሎት በመስጊድ ውስጥ
ፋትዋ ቁጥር 7262፣ በዙ ለ ሂጃ 26፣ 1421 ከሂጅራ በኋላ (ኤፕሪል 5፣ 2000)
የውይይት አጀንዳ፦ በእስልምና መስጊድ ውስጥ የክርስቲያኖች ስብሰባ ወይም ፀሎት ማካሄድ ይፈቀዳልን?
ፋትዋ፦ ለአላሕ ምስጋና፣ ለአላሕ መልዕክተኛና ለአጋሮቹ ደግሞ ፀሎት እና ሰላም ይሁን። በመስጊድ ውስጥ ክርስቲያኖችም ሆኑ ሌሎቹ ካፊሮች ፀሎታቸውን ወይም ሃይማኖታዊ ስብሰባዎቻቸውን ማካሄድ አይችሉም። አንድም ሰው በፀጥታ ሊመለከታቸው ከማይገቡ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ይህ ነው።
አላህ እንዲዘከር በታዘዘበት እና ያም የሚደረገው ለእርሱ ብቻ በሆነበት ሥፍራ እንዲህ ያለው ድርጊት እንዴት ሊፈቀድ ይችላል?
ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል። ማውጣትንም ያወጣችኋል። (ቁርአን 71.18)
አላህ እንድትከበርና ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ (አወድሱት)። በውስጧ በጧትና በማታ ለእርሱ ያጠራሉ። (ቁርአን 24.36)
ቤቱንም ለሰዎች መመለሻና ፀጥተኛ ባደረግን ጊዜ (አስታውስ)። ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ። ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን። (ቁርአን 2.125)
ነብያችን ካባ በዙሪያው እና በውስጡ ካሉ ጣዖታት እንዲፀዳና ሃይማኖት የለሾች በአካባቢው እንዳይገኙ እንዲሁም ከዚህ ዓመት ጀምሮ ሃይማኖት የለሾች የፅድቅ ጉዞ እንዲያደርጉበት ወይም ማንም እርቃኑን የሆነ ሰው በዚያ በማለፍ የካባን ትርጉም እንዳያዛባ አዝዘዋል።
የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡
ከዚህ በላይ የቀረበው ጽሑፍ በእስልምና አገዛዝ ስር ባልሆኑት አገሮች ውስጥ (እስልምና ተዋግቶ እስላም ከሚያደርጋቸው አገሮች) መስጊድ ስላለው ሚና ግልፅ በሆነ ሁኔታ ያስረዳል፡፡ ከዚያም በመቀጠል በተነሱት ጥያቄዎች ላይ የተሰጡት ፋትዋዎች እስልምና ከሌሎች ሃይማኖቶች እራሱን በጣም ያገለለ፣ እራሱን ከሌሎች ልዩ አድርጎ የሚመለከት፣ የበላይነትን ለመያዝ አጥብቆ የሚተጋ መሆኑን ግልፅ ያደርጋል፡፡ በየትኛውም አገርና ሕዝብ መካከል ይገንባ የእስልምና መስጊድም ዓላማ ይህንን ግብ ማድረስ ብቻ ነው፡፡
ከዚህም በላይ በእስላም አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ክርስትያኖችና አይሁዶች “ዲህሚዎች” በመሆናቸው የሚታዩት በተለየ መልኩ ነው፡፡ ዲህሚ የሚለው ቃል በመልስ ለእስላም የእንግሊዝኛው ድረ ገፅ መዝገበ ቃላት answering-islam.org/Index/index.html መሰረት “በእስላም አገር ውስጥ የተጠበቀ ሰው ማለት ነው፡፡ ዲህሚዎች ሊሆኑ የሚችሉትም “የመጽሐፉ ሰዎች (ክርስትያኖች ወይንም አይሁዶች) ናቸው”፡፡ ዲህሚዎች የተወሰኑ መብቶች ሊኖሯቸው ይችላል፡፡ (ከነዚህም ውስጥ) እንደ ሃይማኖታቸው ስርዓት በግል ማምለክ ሲሆን ይህም የሚሆነው የጥበቃውን ክፍያ ማለትም (ጂሃዝ)ን እስከከፈሉ ድረስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የአገሪቱ ዜጋዎች ተደርገው አይቆጠሩም፡፡ የእነርሱም ሁኔታ ሁልጊዜ የውርደት ነው፡፡ (ቁርአን 9.29)፤ መዝገበ ቃሉ በመቀጠል የሚናገረውም፤ “አንድ ሰው የተጠበቁ ሕዝቦች የሚለውን አባባል በሚገባ መረዳት ይኖርበታል፡፡ ከማን ነው የተጠበቁት? ከሙስሊሞች ነውን! ይህም አንድ ማፍያ ቡድን ወደ አንድ ሱቅ መጥቶ ለባለ ሱቁ “ከአሁን ጀምሮ እኛ ነን ጥበቃ የምናደርግልህ አንተም ደግሞ ለምናደርገው ጥበቃ ይህንን ያህል ገንዘብ ልትከፍለን ይገባሃል፡፡ ለራስህ ጥበቃ አንተ መሳሪያ መያዝ አያስፈልግህም፡፡ የአንተን ሃላፊነት እኛ እንይዘዋለን፤” ሊሉ እንደሚችሉት አይነት ሁኔታ ነው፡፡
እስልምናን የማይከተሉ ሰዎችን ዲህሚዎች በማለት ፈርጆ መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶችን መንፈግ፣ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መመልከት ትክክል ነውን? ይህ በቁርአን ላይ የተቀመጠ የእስልምና አገር ሕዝብ የሚያውቀው ግልፅ እውነት ሲሆን ወደ ፊት በእስላም አገዛዝ ስር እንዲሆኑ የታቀዱ ሕዝቦችና አገራት የሚያጋጥማቸው እውነታ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትናም ሆነ በስም ክርስትያን የሆኑ ሰዎች ለሰው ልጅ መሰረታዊ መብቶች ያላቸው አመለካከት ከእስልምና በጣም የተለየ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው በሚኖርት አገር ሁሉ ውስጥ የሃይማኖት፣ የፆታ፤ የዘር፣ የቀለም እና የመደብ ልዩነት ሳይደረግበት በእኩልነት መኖር አለበት የሚለው ዓለም አቀፍ መርሆ ከክርስትና እምነት የመነጨ መሆኑ ማንም የሚያውቀው ነው፡፡ ክርስትና በእግዚአብሔር መልክ ለተፈጠረው የሰው ልጅ አክብሮት አለው፡፡ የክርስትና መልእክት ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር መንግስት ወራሽነት ትልቅ ደረጃ መጥራት ነው፡፡ ይህም የሚቻል የሚሆነው በክርስቶስ የመስቀል ሞት በኩል ብቻ ነው፡፡ ሰዎች ይህንን እምነት ቢቀበሉ ጥቅሙ ለራሳቸው ነው፣ ባይቀበሉ ግን ጉዳቱ የእነርሱ ነው፣ መልእክቱን ለተቃወሙና በኃጢአተኝነታቸው ለሚቀጥሉ የመጨረሻው ቀን ሲመጣ ፍርድ የሚሰጣቸው እራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ክርስትና እምነትን የማይቀበሉ ሰዎች መልእክቱን ስላልተቀበሉ ሰብዓዊ መብታቸው እንዲነፈግ አይደረጉም፡፡ ይህ የክርስትያኖች መሰረታዊ እውነታ በሙስሊሞችም ዘንድ በትክክል የታወቀና ሙስሊም ባልሆኑ አገራት የሚታይ ነው፡፡
በምዕራቡ ዓለም የሚኖሩ ሙስሊሞች ሃይማኖታቸውን ባህላቸውን ስርዓታቸውን ሲያከናውኑ ማንም ሰብዓዊ መብቶቻቸውን አይነካባቸውም፡፡ በምዕራቡ ዓለም ሙስሊሞች መስጊዶቸ ይገነባሉ በሙስሊሞች አገሮች ውስጥ እንኳን አዲስ ቤተክርስትያን መገንባት ቀርቶ ጥንታዊዎቹ ታሪካዊ ቤተክርስትያናትም እየወደሙ ነው፡፡
የሆነው ሆኖ የእኛ ጥያቄ፡ በመስጊዶች ውስጥ የሚደረጉት ማናቸውም ነገሮች ለሙስሊሞች የግል ነፍስና ሕይወት የሚሰጡት ዘለቄታዊና ዘላለማዊ ጥቅም ይኖራል ወይ? የሚለው ነው፡፡ ሙስሊም አንባቢዎች ይህን ጥያቄ በትኩረት እንዲያስቡበት እንወዳለን፡፡ ቀጥሎም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍስን በተመለከተ ሊኖር ስለሚችል ትርፍና ኪሳራ የተናገረውን ከዚህ ቀጥሎ አንብቡና በጥልቅ አስቡበት “ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?” ማቴዎስ 16.26፡፡ ለነፍሳችሁ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅን በተመለከተ የሚኖራችሁን ማንኛውንም ጥያቄ ጻፉልን! እግዚአብሔር ይርዳችሁ፡፡
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ