አጫጭር ዜናዎች
በፓኪስታን የክርስትያን ልጃገረዶች ስቃይ!
በፓኪስታን ሙስሊም ወጣቶች ክርስቲያን ልጃገረድን ጠልፈው ደፍረዋል
አለም አቀፍ የክርስቲያን ተቆርቋሪ ድርጅት (International Christian Concern) ከዋሺንግተን ዲሲ በSeptember 28 አንድ ክርስቲያን ልጃገረድ በሶስት ሙስሊም ወጣቶች ባለፈው ሀሙስ በፓኪስታን ፋይዝልአባድ ያለፈቃዷ ተደፍራለች ሲል ዘግቧል። ጉዳዩ የተከሰተው የ10ዓመት ክርስቲያን ልጅ በ60 አመት አዛውንት በAugust 25 በተደፈረችበት በዚሁ ከተማ ውስጥ ነው። እነዚህ የህፃናትን መድፈር ወንጀሎች በፓኪስታን በፑንጃብ ክልል እየተባባሰ መሆኑን የሚያረጋግጡ ሲሆን በተለይ በክርስቲያኖች ላይ የሚደረገው ጥቃት በአገሪቱ ማህብረሰባዊ ደንብ ውስጥ ለክርስትያኖች በሃይማኖታቸው ምክንያት አናሳና ዝቅተኛ ደረጃ ስለሚሰጧቸው ነው።
ከደሀ ክርስቲያን ቤተሰብ የሆነች ሹሜላ ማሲህ የ17 አመት ልጃገረድ ስትሆን እድሜያቸው 30 ዓመት በሚሆን በሶስት ሙስሊም ወጣቶች በፋይዝል አባድ ወረዳ ቻክ 226፤ September 20 2012 ያለፈቃዷ ተደፍራለች። የወጣቷ አጎት አክራም ማሲህ ለICC እንደተናገረው ሰዎቹ የያዙዋት ሹሜላ እናቷ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ወደምትሰራበት ቤት እየሄደች እያለች ነበር።
«ከቤት ከጠዋቱ 5 ሰአት ወጥታ እናቷ ወደምትሰራበት ቦታ ስትሄድ ነብር ሶስት ሙስሊም ወጣቶች አፍነው አቅራቢ ወዳለው በመሰራት ላይ ወዳለ ቤት የወሰዷት፣ ያንገላቷትና የደፈሩዋት» ሲል ገልጿል።
ከጥቂት ሰአት በኋላ የሹሚላ ወላጆችና አጎቷ አለመኖሯን ሲገነዘቡ ፍለጋ ጀመሩ። «በመሰራት ላይ ያለ ቤትን ስናልፍ የሴት ጩኸት ሰማን ስንደርስም በር ላይ ሁለት ወንዶች ቆመው ነብር። ሹሚላ ቆስላለች፣ ራቁቷን በጨርቅ ከአልጋ ጋር ታስራለች። እኛ ያገኘናት ወደ ከሰዓት በኋላ 11 ሰአት አካባቢ ስለሆነ በእንደዚህ ያለሁኔታ ለስድስት ሰአታት ቆይታለች» ሲል ማሲህ ተናግሮአል።
ማሲህ ጉዳዩን በሳሙንድሪ ቴህሲል በፋይዝልአባድ ክልል ላለው ለታርክሃኒ ፓሊስ ጣቢያ አመልክቷል። ሁለት ተከሳሾች ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በእስር ላይ ናቸው። የአካባቢው ተወላጅ የመብት ተሟጋች ለICC እንዳለው ብዙ ሙስሊሞች ከክርስቲያኖች ጋር በመቆም በወንጀለኞች ላይ አፋጣኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል ብሏል።
«እነዚህ ሰዎች በህግ መቀጣት አለባቸው፤ ማንንም ወጣት ልጀገረድ መድፈር ትክክል አይደለም። እነዚህ ሰዎች አውሬዎች ናቸው እና መቀጣት አለባቸው» ሲል ማንዙሪ ማሲህ የሹሚላ አባት ለAsia News ተናግሮአል።
የሹሚላ ጉዳዩ የተከሰተው የ60 አመት አዛውንት ሙሃመድ ናዚር ድሆች በሚኖሩበት በዩሱፍ አባድ በፋይዝል አባድ ክልል ባለፈው ነሀሴ የ10 አመት ክርስቲያን ልጅ ከደፈረ በኋላ ወር ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነው። ገበያ ለሸጠችው እቃዎች ሂሳብ ቤት ይሰጥሻል ስለተባለች ህፃኗ ናዝሪንን ተከትላ ወደ ቤቱ ሄዳለች ሲል Asia News ዘግቦአል።
የራክሂያ አባት ሳርፍራዝ ማሲህ ጥቂት ጊዜያት ካለፈ በኋላ ሲያገኛት «መሬት ላይ ተዘርግታ በሃይል ስለተደፈረች ደም ይፈሳት ነበር»፤ ማሲህ «እኛ ድሆች ስለሆንን እንዲህ ያሉ ሃብታሞችን ልንቋቋም አንችልም» ብሏል። ናዚር ማሲህን ይህን ለፖሊስ ካሳወቅህ «ክርስቲያኖች ይከፍሏታል» ሲል ተደምጦል።
ሌላው World Vision in Progress የዘገበው ጉዳይ ደግሞ አንድ ክርስቲያን ልጅ እድሜዋ 15 አመት የሚሆናት ሱምባል ማሲህ ላሆር ውስጥ በSeptember 14 በእስላም ቀጣሪዎቿ «በብረት ዘንግና በብረት ቧንቧ ክፉኛ ተደብድባለች» ሲል ነበር። ሱምባል ከዚያ ጊዜ በኋላ የት እንዳለች እስከ አሁን አይታወቅም።
እንደ Society for the Protection of the Rights of the Child መረጃ በፑንጃብ ክልል በ2012 የመጀመሪዎቹ አምስት ወራት 40 የሃይል መድፈር፣ 14 የግድያ፣ 22 የአፈናና 6 የግዴታ ጋብቻ በህጻናት ላይ ደርሷአል። ክርስቲያኖችና የሌሎች አናሳ የሃይማኖት አባላት ሂንዱንም ጨምሮ ሰለባዎች ሆነዋል።
«አናሳ ሃይማኖቶችና የተገለሉ ማህብረሰቦች ሃብታም በሆኑ የገጠር ባለ ርስቶች ተጠቂ ናቸው» ሲል ቄስ ቦኒ ሜንዴስ በፓኪስታን የቀድሞ የNational Commission for Justice and Peace ዋና ጸሐፊ ተናግሮአል። በመቀጠልም «ሹሚላን በግል አውቃታለሁ ምክንያቱስ የአካባቢው ቄስ ነበርኩና። ድሃ ቤተሰብ ቢሆኑም በክርስትና እምነታቸው ጠንካሮች ናቸው ስለዚህ ፍትህ ይገባቸዋል» ብሏል።
የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡
በፓኪስታን እና በተመሳሳይ የሙስሊም አገሮች ውስጥ ከክርስትያን ቤተሰብ ውስጥ የሆኑ ህፃናት ልጃገረዶች ለምን ይደፈራሉ? ይህ ስነ-ምግባራዊ ነውን? የሙስሊም ቤተሰብ ልጃገረዶች እንደ ክርስትያኖቹ ተደፈሩ የሚል ዜና በብዛት አይሰማም፣ ሙስሊሞች ስለምን ይህንን በማድረግ በክርስትያኖች ላይ ግፍን ይፈፅማሉ?
ለእነዚህ ጥቄዎች መልስ ሊሆኑ የሚችሉ ጥቂት ነገሮችን እንደ መልስ ሐሳብ መሰንዘር ይቻላል፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ እምነቱ ይፈቅድላቸዋል ወይንም ይህንን እንዲያደርጉ ያዛቸዋል፡፡ አለበለዚያም ሙስሊሞችን እንዲህ ዓይነት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን እንዳይፈፅሙ የሚከክላቸው የስነ-ምግባር መርሆ፣ የሕግ ስርዓት የላቸውም የሚሉት እንደ አማራጭ ሐሳቦች ሊሰነዘሩ ይችላሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱሳዊው ክርስትና ግን እንደዚህ ዓይነት ነገሮች በፍፁም ካለመፍቀዱም ባሻገር እንኳን ህፃናትንና ያላገቡትን መድፈር ቀርቶ ከጋብቻ ውጭ የሚደረገውን ማንኛውንም የግብረ ስጋ ግንኙነት አያበረታታም፡፡
ከዚህም ባሻገር የሰው ልጅ በውስጡ ያለውም ህሊና እንደዚህ ዓይነቱን ድርጊት ከመፈፀም ሊከለክለው ይገባል፡፡ በእርግጥ አሁንም በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ሕሊና በአንድ ሰው ውስጥ ሊሰራ የሚችለው ሰው ሕሊናው የሚለውን ሲያዳምጥ ነው፡፡ ሕሊና በሰው ውስጥ እንደ ዳኛ እና መብራት በመቀመጥ ጭለማን ከብርሃን ክፉን ከበጎ የሚለይ እራሱን የቻለ ዳኛ ነው፡፡ ሰዎች ሕሊናቸው እንዲሰራና ወደ መልካም እንዲመለሱ እግዚአብሔር ሕሊናቸውን ሊያነቃላቸው ይገባል የሰው ልጅ ህሊና የኃጢአት እስረኛ ሆኗልና፡
ይህ የሚገኘው ሰው በኃጢአቱ ተናዞና በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ካገኘና ከፀደቀ ብቻ ነው፡፡
የዚህ ገፅ አዘጋጆች አንባቢዎችን ሁሉ የሚጋብዙት ሕናቸውን በኃጢአት ከታሰረበት ቦታ ወጥቶ ነፃነት ወደሚያገኝበት ወደ እግዚአብሔር እምነት እንዲመጡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያነቡና ሕይወታቸውንም እንዲመረምሩ ነው፡፡
እግዚአብሔር ይርዳችሁ፡፡