ሙስሊም በእርግጥ ማወቅ ይችላልን?

Joseph Abraham from Egypt

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

ለክቡር ሙስሊም ወዳጄ

እራሴን ላንተ እንዳስተዋውቅህ ፍቀድልኝ፡፡ ስሜ ዮሴፍ አብርሃም ነው ቀድሞም እጠራ የነበረው መሐመድ ካማልኤልደን ሙጃሂድ ተብዬ ነበር፡፡ ከብዙ ዓመታት ፍለጋ በኋላ እውነት ጋ መጥቼያለሁኝ፣ እኔም የማምነው እግዚአብሔር ለእኔ በቅዱስ ቃሉ - በመጽሐፍ ቅዱስ በኩል ያደረገልኝን ለሌሎች እንዳካፍል እግዚአብሔር እንደመራኝ ነው፡፡ የእኔንም ደብዳቤ በምታነቡበት ጊዜ እባካችሁን ትዕግስት ይኑራችሁ፡፡

እኔ በትውልድ ግብፃዊ ነኝ የተወለድሁትም በሙስሊም ቤተሰብ ውስጥ ነው፡፡ አባቴ የሙስሊም ቄስ (ሸኬ) እንዲሁም በግብፅ በካይሮ ውስጥ እስከሞተበት ጊዜ ድረስ የእስልምና አስተማሪ ነበር፡፡ ቤተሰቤም በእስልምና ዝርያቸው ይመኩ ነበር፣ ምክንያቱም የቀደሙት ዘሮቻችን በሙሉ የሙስሊም ካህናት ነበሩና፡፡ ስለዚህም ቤተሰቦቼ ወደ ቁራን ትምህርት ቤት በስድስትና በሰባት ዓመት ዕድሜዬ ልከውኝ ነበር፡፡

እኔም ገና ትንሽ እያለሁኝ ስለእግዚአብሔር ጥያቄዎችን ማለትም ስለፍርዱ፣ ስለ እውነቱ፣ ስለ የሰው ልጅ የዘላለም መጨረሻ  እና ወ.ዘ.ተ መጠየቅ ጀምሬ ነበር፡፡ ገና ትንሽ ልጅ ስለነበርኩኝም በጥያቄዎቼ ላይ ሌሎቹ ያሹፉቧቸው ነበር፡፡ እንዲህ ዓይነቱም ነገር ምንም ጥቅምን አላመጣም ነገር ግን ተስፋ እንድቆርጥ አደረገኝ፡፡ በተስፋ መቁረጥና በጭንቀትም ውስጥ እንድኖር አደረገኝ ምክንያቱም ነፍሴ እስልምና ሊሰጠው የማይችለውን አንድ ነገር ትፈልግ ነበርና ነው፡፡

የእኔም የእስልምና መሰረት ውጪያዊና ጥልቀትም ያልነበረው ነበር፡፡ አባቴም እንደ አንድ ሼክ ቁርአንን በሙሉ በቃሉ ያስታውሰው ነበርና እኔንም እንደ እሱ እንዳደርግ ያበረታታኝ ነበር፡፡ ይህም ደግሞ ይግባኝም - አይግባኝምም ነበር፡፡ ስለዚህም እኔ በደረቁ የሃይማኖት ልጅ ሆኜ ልቤ ግን ልክ እንደ በረሃ ድርቅ ያለ ነበር፣ ያም ደግሞ ይመስል የነበረው ምንም ማለቂያ የሌለውና ተስፋ አስቆራጭም ነበር፡፡

ልክ እንደ ብዙዎቹ ሙስሊሞች ኖር የነበረው በባህላዊ የሙስሊሞች ጉርብትና ውስጥ ነበር፡፡ ይህም በቀን የአምስት ጊዜ እንደ መብረቅ በሚጮኸው የአላህ አምልኮ ጥሪ ውስጥ እኖር ነበር ማለት ነው፡፡ የእስልምናንም የሃይማኖት በዓላት በሃይማተኝነት እናከብራቸው ነበር፡፡

እምማር የነበረውም እስላም የአይሁድን እና የክርስትናን እምነት የተካ የመጨረሻ ሃይማኖት ነው እየተባልኩ ነበር፡፡ ክርስትያኖችም ሦስት አምላክን እንደሚያምኑም ይነገረኝ ነበር፡፡ ከዚህም በላይ ክርስትያኖች የመጀመሪያውን መጽሐፍ ቅዱስ እንደበከሉት ተምሬያለሁ፡፡ የመጀመሪያው መጽሐፍ ለእስላሙ ነቢይ ለመሐመድ ማገናዘቢያ የሆነውን ነገር ይዞ እንደነበረ የሚታሰበው ማለት ነው፡፡ እስልምና የኢየሱስ ክርስቶስን ሞት መቀበርና መነሳትንም ይክዳል፡፡ ነገር ግን እንደዚህ ዓይነት ክህደቶችን ለማድረግ ምንም እርግጠኛ የሆነ መሠረታዊ መግለጫ ወይንም ማብራሪያን ለመስጠት አጥጋቢ ሙከራ ተደርጎ አያውቅም ነበር፡፡

ወደ ወጣትነት ደረጃም ስደርስ የትኛው ሃይማኖት ትክክል እንደሆነ ለማወቅ ያለኝ ፍላጎት በጣም እየጨመረ መጣ፡፡ የእስልምናን እምነት መጠየቅ በሙስሊም አገር ውስጥ ትዕግስት ስለማይሰጠው የኔ ጥያቄና ምርምር የተመሠረተው በግል ሆነ፡፡ ነገር ግን ቆይቶ  የኔን ጉጉት ብዙዎች አወቁት፡፡ እነሱም በእኔ ላይ እጅግ መጥፎ ክስን ወረወሩ፡፡ እኔም ‹በአዕምሮው ያልተረጋጋ› እንዲሁም ደደብና የማይረባ ተብዬ ተጠራሁኝ፡፡ አሁንም ሌሎች ደግሞ እኔ በፀረ እስላም ድርጅት ተፅዕኖ ስር እንዳለሁ ይናገሩ ነበር፡፡ ሙስሊሞች ሕይወቴን የማይቻል ስላደረጉትም መሞትን ሁሉ ተመኝቼ ነበር፡፡ ነገር ግን ማወቅ እፈልግ የነበረው እውነቱን ብቻ ነበር፡፡

በሃያዎቹ ዓመታቴ ጅማሬ ላይ እንደገና ምርምሬን ቀጠልኩኝ፡፡ እኔንም በጣም ያሳስቡኝ ከነበሩት ጥያቄዎቼ መካከል፡- ከሞት በኋላ የት ነው የምሄደው? የዘላለም መግቢያዬን ለማወቅ መብት የለኝምን? ሙስሊሞች ለምንድነው ስለራሳቸው ሃይማኖት መወያየትን እንደዚህ በጣም የሚቃወሙት? እግዚአብሔር ሰዎች ስለመጨረሻቸው እውራን እንዲሆኑ ይፈልጋልን? እስልምናስ ብቸኛው እውነተኛ ሃይማኖት ለመሆኑ በምንድነው የማውቀው?

ከማንም ምንም እርዳታን ሳላገኝ ስለ ፍልስፍና መጻሕፍት ማንበቤን ጀመርኩኝ አንዳንዶቹም ክህደትን የሚገፋፉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርን መካድ እውነትን ለማወቅ ያለውን የውስጥ ጥማት ፀጥ ሊያሰኘው በፍፁም አይችልም፡፡ እኔም የዕድልን እና የግዴለሽነትን አመለካከት እንድይዝ ተበረታትቼ ነበር፣ ነገር ግን አሁንም ይህ ነገሮችን የበለጠ አጠናከረብኝ፡፡ ነፍሴ አሁንም እጅግ በጣም እየፈለገች የነበረችው የኛን የመንፈሳዊ መጨረሻ መድረሻንና የእግዚአብሔርን የዘላለም እውነት ለማወቅ ነበር፡፡

እኔም ሙስሊም ተብዬ የተቆጠርኩት ከሙስሊም ወላጆች በመወለዴና በሙስሊም አገር ውስጥ በመኖሬ መሆኑን ማወቄ ብቻ በጣም ያስቸግረኝ ነበር፡፡ ለእኔም ምንም ምርጫ፣ እውነቱንም ለመመርመርና ለማግኘት  ምንም ዕድልም አልተሰጠኝም ነበር፡፡ ከሁሉም በከፋ መንገድ የማውቀው (የኔንም ቤተሰብ ጨምሮ) በዘር ብቻ ሙስሊም መሆናችንን ብቻ ነበር፡፡ ለእውነት ልባቸውን ክፍት በማድረግ ሃይማኖቱን ለመመርመር በእውነት ትጋት ያለውን ጥረት ሲያደርግ ማንንም ሙስሊም  በፍፁም አላየሁም፡፡

በ1968 ዓ.ም አንድ መጽሐፍ እያነበብኩኝ እያለ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ጥቂት ቁጥሮችን አገኘሁኝ እነሱም በጣም ትኩረቴን ሳቡት፡፡ እነዚህ ቁጥሮች ስሙ ኢየሱስ ስለተባለ አንድ ሰው በስልጣን ይናገራሉ፡፡ ቃሎቹም የሚሉት ይህ ሰው ‹ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።› ዮሐንስ 14.6 ማለቱን ነው፡፡

እጅግ በጣም ብዙ ጥቄዎችም ወደ አዕምሮዬ ይመጡ ነበር፣ ከዚያም የእስላም ነቢይስ? ሙስሊሞች ስለ ኢየሱስ በዚህ መንገድ በጭራሽ ለምን አይናገሩም? እነሱ ሁልጊዜ የሚናገሩት ስለ እስላም ነቢይ ብቻ ነው፡፡ አብ የሚባለውስ ማነው? እግዚአብሔርስ እንዴት አባት ተብሎ ሊጠራ ይቻላል? የእሱስ (የእግዚአብሔርስ) ሚስት ማናት? የመጨረሻ እውነት እንደሆነ ስለ እራሱ የሚናገረው እስልምናስ? ከዚህም ሁሉ በላይ እኔ እንዴት አድርጌ መጽሐፍን ቅዱስን ልታመንበት እችላለሁኝ? ምክንያቱም ሙስሊሞች የተበላሸ፣ የተበከለ ነው ይሉታልና፡፡ እናም ሌሎችም በጣም ብዙ ጥያቄዎች፡፡

ያንኑ መጽሐፍ እያነበብኩኝ እያለሁ በዚሁ ኢየሱስ በተባለው ሰው የተነገረ ሌላ ዓረፍተ ነገር ላይ መጣሁኝ:- ‹እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።› ማቴዎስ 11.28፡፡ እኔ ለዘመናት እረፍትን ስፈልግ ነበር የኖርኩት ይህ ኢየሱስ የእረፍት ምንጭ እንደሆነ ነው የሚናገረው ስለዚህም ሌሎችን ወደ እርሱ እንዲመጡ ነው የሚጋብዘው፡፡

በዚያንም ሰዓት መጽሐፍ ቅዱስ የሚባል ነገር የለኝም ነበር፡፡ አንድም መጽሐፍ ቅዱስ አይቼም አላውቅም ነበር፡፡ ከዚያም እንዲህ ስለ እራሱ በስልጣን ስለሚናገረው ሰው የበለጠ አንብቤ ለመረዳት እንድችል ክርስትያን ነኝ የሚልን አንድን ሰው በሚስጢር መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያውሰኝ ጠየቅሁኝ፡፡

በዚያኑ ሰዓትም አንድ አሜሪካዊ ወንጌላዊ ግብፅን ይጎበኝ እንደነበረ ሰማሁኝ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስንም መልእክት ለመስማት በትልቅም ጉጉት ሆኜ በፕሮቴስታንት ቤተክርስትያን ውስጥ በምስጢር ሰርጌ ገባሁኝ፡፡ እሱም ምንም አረብኛ ስለማያውቅ በአስተርጓሚ ነበር የሚናገረው፡፡ ከዚህ በፊት ሰምቻቸው የማላውቃቸውንም ነገሮች ሰማሁኝ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም የዘላለም እውነት ምንጭ የሆነ መጽሐፍ መሆኑን ከዚህ በፊት አላውቅም ነበር፡፡

ባለፉት ጊዜያት ቁርኣንን አንብቤ የቁርኣንን ክፍሎች በቃሌ ይዤ ነበር፡፡ እስልምናንም ለዓመታት ተምሬ ነበር ነገር ግን እግዚአብሔር በትምህርቶቹ (በቅርኣን) ውስጥ ለእኔ በፍፁም ተናግሮኝ አያውቅም ነበር፡፡ በተቃራኒው ግን መጽሐፍ ቅዱስን ሳነብና ከመጽሐፍ ቅዱስም ላይ መልእክትን ስሰማ ልዩ የሆነ ድምፅ ልዩ በሆነ ስልጣን ለእኔ ሲናገረኝ መስማት ጀመርኩኝ፡፡

ስለዚህም ወደ ሰባኪው ለመሄድና ስለ ክርስቶስና ስለመጽሐፍ ቅዱስ የበለጠ እንዲናገረኝ ለመጠየቅ ብርታትን አገኘሁ፡፡ እሱንም አንድ ሙስሊም ወደ መጽሐፍ ቅዱስና ወደ ሰማያዊው አባት መቅረብ ይችል እንደሆነ ጠየቅሁት፡፡ እኔ እራሴም በእርግጥ ስለዘላለም ሕይወት ማወቅ እችላለሁን? ስለ ኃጢአት ይቅርታ ከሲዖል ስለማምለጥ እና የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆን በእርግጥ ማወቅ እችላለሁን?

ሰባኪውም ዮሐንስ 3.16 አካፈለኝ ‹ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።› ይህ ጥቅስ ብቻውን ለዓለም ሃይማኖቶች ሁሉ መልስ አለው፡፡ በሰው ልጆች ኃጢአት የተነሳ እግዚአብሔር ልጁን ለኃጢአተኞች እንዲሞት ወደ ዓለም ላከው፡፡ ከዘላለም ሲዖል ጥፋት ለማምለጥ ይህን እውነት ብቻ ማመንን ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔር ይህን ያደረገውም ከፍቅርና ከእርሱ መልካም ልብ አመንጭቶ ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ እራሱ ፃድቅ ፈራጅም ከመሆኑ የተነሳ ነው፡፡ የእግዚአብሔር የፅድቅ ፍርድ የኃጢአትን መቀጣት ይጠይቃል፡፡ ‹የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነውና› ሮሜ 6.23፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ምህረትን የተሞላም ነው ለዚህ ነው ይህን አማራጭ የሰጠን ‹የእግዚአብሔር የፀጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው› ሮሜ 6.23፡፡

ቀላል እውነት ነው፣ እውነት ያልሆነ ይመስላል ነገር ግን እውነት ነበር ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ነውና፡፡ እኔም እግዚአብሔር ለእኔ እያደረገ ያለውን ጥሪውን ልዘጋው አልቻልኩኝም -- ‹ና ወደኔ … ና ወደኔ ና … ና› እያለ የሚጠራኝን፡፡ ‹ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት፥ አባቶቻችሁ እኔን የፈተኑበት የመረመሩበትም አርባ ዓመትም ሥራዬን ያዩበት በምድረ በዳ በፈተና ቀን በማስመረር እንደ ሆነ፥ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።› ዕብራውያን 3.8-9፡፡ እናም መጽሐፍ ቅዱስን በጣም ባነበብኩና ጥቅሶቹንም በሰማሁ ቁጥር እግዚአብሔር ለግሌ እየተናገረኝ ለመሆኑ እያመንኩኝ ሄድኩኝ፡፡

የእግዚአብሔርም ቃል ለልቤ መናገሩን ቀጠለ፣ ‹እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን?›  ዕብራውያን 2.2፡፡ ኃጢአተኞች ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ ማን መሆኑንና እሱ ለእነሱ ምን እንደሰራ ካላወቁ በስተቀር ከዘላለም ፍርድ ማምለጫ ሌላ ምንም መንገድ የላቸውም፡፡ እግዚአብሔርም ለእኔ ማስጠንቀቂያንም እየሰጠኝ ነበር ምናልባት እኔ ቃሉን ከማመን ባመነታ፣  ከዚያም 2ቆሮንቶስ 6.2 ላይ ያለውን ቃል ‹እነሆ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው እነሆ የመዳን ሰዓት አሁን ነው› ያም የሚለው ነገ በጣም ይዘገያል ነው፡፡ የክርስቶስን አዳኝነት ማለትም እግዚአብሔር በቀራኒዮ መስቀል ላይ የእኛን ቦታ እንዲወስድ ልጁን መላኩን አለመቀበል የእግዚአብሔርን ፍርድ በራስ ላይ ማምጣት ማለት ነው፡፡ ታዲያ ሌሎች ሃይማኖቶች ምንም ሊያስተምሩ ቢችሉ በእውነት ግድ ሊለን ይገባናልን? አይገባም፡፡ ለምን? ምክንያቱም የእግዚአብሔር የዘላለም እውነት አይለወጥምና፡፡

በመጨረሻ ከዓመታት የስቃይ ትግል በኋላ ወደ እውነቱ ተመራሁኝ፣ ወደ ጌታ፣ ወደ እኔ አዳኝ፣ ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመራሁኝ፡፡ እሱ እግዚአብሔር ነው፣ እሱ እውነት ነው፣ እሱ የሕይወት ሰጪ ነው፣ እሱ ብቻ ነው ወደ ደኅንነት የሚወስደው ብቸኛው መንገድ፡፡

ውድ ሙስሊም ወዳጄ ሆይ አስታውስ አንድ ቀን እራስህ ብቻህን በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ትቆማለህ፡፡ የእግዚአብሔርን ፍርድ ልታቋቋመው ትችላለህን?

ክርስትያኖች -- ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው የሚያምኑቱ በእግዚአብሔር ፍርድ ስር በፍፁም (ከዚህ በኋላ) አይደሉም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በክርስቶስ ሰውነት ውስጥ አንድ ጊዜ ፈርዶባቸዋልና፡፡ እሱም ስለ እነሱ ሞቷል፣ ለነገሩ ለአንተም ነው እሱ የሞተው፡፡

እስኪ ልጠይቅህ አሁን አንተ ኃጢአተኛ መሆንህንና እንዲያድንህ ክርስቶስን የምትፈግል መሆንህን ለእግዚአብሔር ከመናገር የሚከለክልህ ምንድነው? እሱን እንደ አዳኝህ አሁኑኑ ተማመነው፡፡ ከዚያም ለክቡር ነፍስህ መዳን በሰማይ ትልቅ ደስታ ይሆናል፡፡

እግዚአብሔር ባሪያውን ሰባኪውን ከሰማይ ልኮ ወደ ክርስቶስ እስከመራኝ ድረስ እኔ እውነቱን ለዘመናት ስፈልግ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ለአንተም አሁን ያንን እያደረገ ነው፡፡ አንተም እውነቱን ልታውቅና እኔ ያገኘሁትን እና ያለኝን የመንፈሳዊ እውነተኛ ነፃነት ልታውቅ ትችላለህ፡፡ ‹እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።› ዮሐንስ 8.32፡፡

ክቡር ወዳጄ ሙስሊም ሆይ! በክርስቶስ በጌታችን ወዳገኘነው መንፈሳዊ ነፃነት ውስጥ ናና ተቀላቀለን፣ ምስክነትንም ካንተም እንስማ ካንተ ጋርም ደስ እንሰኛለን፡፡

ከአክብሮት ጋር፡፡   

Joseph Abraham

 

የትርጉም ምንጭ: Can a Muslim know for sure?

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ