የሴቶች ቦታ በንፁህ እስልምና
ክፍል ዘጠኝ - ከበፊት ጋብቻዋ ያገኘችውን ልጇን እንዳትንከባከብ ባል ሚስቱን የማገድ መብት አለው፡፡
[ክፍል አንድ] [ክፍል ሁለት] [ክፍል ሦስት] [ክፍል አራትና አምስት] [ክፍል ስድስት] [ክፍል ሰባትና ስምንት] [ክፍል አስር]
በ M. Rafiqul-Haqq and P. Newton
ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ
በጥሎሽ አማካኝነት የግብረ ስጋ ግንኙነት መብት የተጠበቀ ነው የሚለው ነገር ከበፊት ጋብቻ የተገኙትን ልጆች እስከ ማጥቃት ድረስ ሄዷል፡ ‹ሚስቱን ከበፊት ባሏ የወለደቻቸውን ልጆቿን ከመንከባከብና ጡትንም ከማጥባት ለመከልከል ባል መብት አለው (እርሷ በባሏ ቤት ውስጥ የምትኖር ከሆነ) ምክንያቱም እርሷ ባሏን እንዳትንከባከብ በጣም ስራ ያበዛባታልና፣ እንዲሁም የእርሷን ውበትና ንፅህናም ያቃውሳልና እነዚህ ሁሉ ነገሮች የባል ብቻ መብቶች ናቸውና› 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al-'Elmeyah, 1990, vol. 4, p. 488.(ሃኒፋይትስ)፡፡
የሚስቱን የዕለት መኖሪያ ወንድ የመከልከል መብት አለው፡ በእስልምና ‹ጋብቻ በባልና ሚስት መካከል ምንም የጋራ የሆነ ንብረትን አያፈራም› Encyclopaedia of Islam, under 'Nikah'፡፡ ስለዚህም ሚስት በየዕለቱ መደገፍ ያለባት ባሏ በሚሰጠው ድጋፍ (እርዳታ) ላይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች እንደሚጠቁሙት ባልየው ሚስቱን ከመርዳት ፈቃደኛ የማይሆንባቸው እጅግ በጣም ብዙ ምክንያቶች አሉ፡ ይህንን በተመለከተ ሐኒፋውያን የተናገሩት፡ ‹ሴትን የመርዳት (ናፋቃ) ነገር በወንድ ላይ ግዴታ ነው ምክንያቱም ሴቲቱ በወንድየው ቤት ውስጥ የተዘጋባት ናትና፣ እንዲሁም የእሱ ብቻ፣ ማለትም ለእርሱ ብቻ የተለየች ናትና› 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al-'Elmeyah, 1990, vol. 4, p.495፡፡
‹ሐኒፋውያን አሉ፡ ከሚከተሉት ነገሮች የተነሳ ለሴት ምንም እርዳታ አይኖራትም ይህም እርሷ፡
1. ዐመፀኛ (ናሺዝ) ከሆነች ነው ማለትም ባሏ ሳይፈቅድ ወይንም ደግሞ አሳማኝ ምክንያት ሳይኖራት ከቤት ውጪ ለምትወጣ ሴት ነው፡፡ ወይንም እራሷን ለእርሱ ማስገዛት እምቢ ካለች ነው ስለዚህም ወደ እርሱ ቤት መግባት የለባትም፡፡ ነገር ግን የግበረ ስጋ ግንኙነት ከማድረግ እምቢ የምትል ከሆነ (ያ ምንም እንኳን ሕገ ወጥ ቢሆንም) ተቃውሞውም እርሷን ከመርዳት ለማቆም ምክንያት አይሆንም፤ ምክንያቱም እርሷን ለመርዳት ብቁው ምክንያት እርሷ በቤት ውስጥ የተዘጋባት በመሆኗ ነውና›፡፡
2. ከዳተኛዋ ሴት ከሆነች፡፡
3. የባሏን ወንድ ልጅ ወይንም አባት የምትታዘዝ ሴት ወይንም ከሁለቱ አንዱን በምኞት የምትስም ወይንም ከባሏ ጋር ያላትን ግንኙነት ሊያግድ የሚያስደርስ ማንኛውንም ነገር የምታደርግ ከሆነ፡፡
4. የጋብቻ ውሏ ትክክል ያልሆነ ሴት እንዲሁም ከሌላ ወንድ ጋር ማለትም ወንድየው እርሷን ሚስቱ እንደሆነች በስህተት አስቦ የግብረ ስጋ ግንኙነትን ያደረገች ሴት ከሆነች፡፡
5. የግበረ ስጋ ግንኙነትን ለማድረግ በጣም ገና ልጅ የሆነች ሚስት ከሆነች፡፡ (የእስልምና ሕግ ለሕጋዊ ጋብቻ የዝቅተኛ ዕድሜ ገደብ ሕግ አያውቅም) Encyclopaedia of Islam, under 'Nikah'፡፡
6. ምንም እንኳን እርሷ ምንም በደል የሌለባት ብትሆንም፣ በእስር ቤት ውስጥ ያለች ሚስት ሆና እርሱ ወደ እርሷ መግባት (እንደ ሚስቱ) የማይችል ከሆነ፡፡
7. ከከፍተኛ ሕመም የተነሳ የታመመች ሚስት ከጋብቻው ስርዓት በኋላ ወደ ባሏ ቤት ያልገባች፣ ምክንያቱም እርሷ ለባሏ እራሷን ባለማስገዛቷ የተነሳ፡፡
8. በሌላ ወንድ ተደፍራ የነበረች ሚስት ከሆነች፡፡
9. ወደ ሐጂ ጉዞ ያደረገች ሚስት በቤት ውስጥ ስላልተዘጋች ለእርሷ ምንም እርዳታ አይደረግላትም 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al-'Elmeyah, 1990, vol. 4, pp. 495-497፡፡ የሚሉት ነጥቦች ይገኙባቸዋል፡፡
የኢማም ሻፊ ተከታዮች የተናገሩት፡ ‹ለሚስት የሚደረግ እርዳታን የሚወስኑ ሁኔታዎች እንደሚከተሉት ናቸው፡
በአንደኛ ደረጃ፡ እርሷ እራሷን ለእርሱ ማቅረብ አለባት፣ ይህም ለእርሱ እንደሚከተለው በማለት ነው፡ ‹እኔ እራሴን ለአንተ አስረክባለሁኝ› በጣም ጠቃሚው ነገርም ከእርሱ ጋር ለመገናኘት ዝግጁ መሆኗንና እርሱ እንደፈለገውም ወደ እርሷ የመግባቱን ነገር አስቀድማ ማስታወቅ ይኖርባታል፡፡ ዝግጁ መሆኗን ለእርሱ የማታስታውቅ ከሆነ፣ እርሷ ድጋፍን የማግኘት ምንም መብት ሊኖራት አይችልም፣ ይህም እርሱ ከእርሷ ጋር ለመገናኘት ያቀረበውን ጥያቄ ባትቃወምም እንኳን ነው፡፡ ስለዚህም እርዳታ (ድጋፍ) የተመሰረተው በሁኔታዎች ላይ ነው እርሷ እርሱ በፈለገበት ጊዜ ሁሉ እንዲገናኛት ፈቃደኛ መሆኗን በማስታወቋ ላይ የተመሠረተ ነው፣ እንዲሁም እርሱ በፈለገበት ጊዜ ሁሉ እራሷን ለማቅረብ ፈቃደኛ በመሆኗም ላይ ነው፡፡ ስለዚህም በቀን እየሰራች ቢሆን እናም እርሱ ሊያገኛት ባይችል ለእርሷ የሚደረገው ድጋፍ ሊነፈጋት ይችላል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ፡ እርሷ የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ ችሎታ ሊኖራት ይገባል፡፡ እርሷ ትንሽ ልጃገረድ ብትሆን፣ የግብረ ስጋ ግንኙነትን ማድረግ የማትችል ቢሆን እርሷ ለእርዳታ ብቁ ልትሆን አትችልም፡፡
በሦስተኛ ደረጃ፡ እርሷ ዓመፀኛ መሆን የለባትም፣ ያም ባሏን የማትታዘዝ መሆን አይኖርባትም፣ ይህም እርሱምን በእርሷ ከመደሰት፤ እርሷን ከመንካት፤ ከመሳም እና የግብረ ስጋ ግንኙነትን ከማድረግ የሚያግደው እምቢተኝነትን ሁሉ ይጨምራል፡፡ እርሷ ከዚህ በላይ ያሉትን ማንኛውንም ነገሮች እምቢ ብትለው ለዚያን ዕለት የሚሰጣት ድጋፍ ይነፈጋታል፣ ምክንያቱም ድጋፉ የሚደረገው በየቀኑ ነውና .. የአንድ ቀንም ዓመፀኝነት የእርሱን ስጦታ (ድጋፍ) ያስቀረዋል ያም ለእርሷ ለወቅቱ የሚያስፈልገውን ልብስ ሁሉ በማስቀረት ጭምር ነው፡፡ 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al-'Elmeyah, 1990, vol. 4, pp. 498፡፡
የኢማም ማሊክ ተከታዮችም እንደሚከተለው አሉ፡ አንድ ወንድ ለሴት የሚሰጠው ድጋፍ ሁኔታ እርሷ እራሷን ለግብረ ስጋ ግንኙነት በማቅረቧ ላይ የተመሰረተ ነው፣ ስለዚህም እርሱ ይህንን ከእርሷ የሚጠይቅ ከሆነ እርሷ እምቢ ልትል አትችልም፡፡ ካለበለዚያ እርሷ ለድጋፉ ምንም መብት ሊኖራት አይችልም› 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al-'Elmeyah, 1990, vol. 4, pp. 497-498፡፡
የኢማም ኢብን ሐናባል ተከታዮችም እንደሚከተለው አሉ፡ ‹የሚስት የቀን ድጋፍ በባሏ የተነሳ ነው፣ እርሷ ለባሏ ሙሉ ለሙሉ እራሷን ከሰጠች ከባሏ የግብረ ስጋ ግንኙነት ደስታ ምላሽ እንዲሆን ለእርሷ እርሱ የእለት ድጋፍ ይሰጣታል፣ ስለዚህም ሚስት እራሷን ሙሉ ለሙሉ ከሰጠች የዕለት ድጋፍ መሰጠቷ የግድ ነው፤ ይህም እርሷ ዘጠኝ ዓመት እድሜ እስከደረሰች ድረስ ነው፡፡ ስለዚህም እርሷ በአካል ጤናማ እስከ ሆነችና እራሷንም ለባልየው የግብረ ስጋ ግንኙነት ደስታ እስካልሰጠች ድረስ ለእርሷ የዕለት ድጋፍን ለማግኘት ምንም መብት አይኖራትም፡፡ በመሆኑም ሚስትየው እራሷን ለመስጠት እምቢ ካለችና ባልየው የግብረ ስጋ ግንኙነትን ማድረግ ከእርሷ ጋር ባይችል የእለት ድጋፏ ይቋረጣል፡፡ እርሷ ከባሏ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ከማድረግ የሚያግዳት ችግር ቢኖርባት፤ ከዚያ በኋላ ለባሏ በሕመም ውስጥ እስከሆነች ድረስ የዕለት ድጋፏ ሊሰጣት አይችልም ይህም ለእርሷ እንደ ቅጣት ነው ምክንያቱም እርሷ በጤንነት በነበረችበት ጊዜ ለባሏ እራሷን ለመስጠት እምቢ ብላለችና› 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al-'Elmeyah, 1990, vol. 4, pp. 497-499፡፡
ከዚህ በላይ ያሉት ሕግጋቶች በእውነት ከአላህ የመጡ ተደርገው የሚታመንባቸው ናቸው፡፡ ጋዚሪ የተለያዩ የእስልምናን ትምህርት ቤቶችን ሕግጋት አመለካከትን በማጠቃለል በስራው መግቢያ ላይ የተናገረውን አል ፊክ የጻፈው እንደሚከተለው ነው፡ ‹የኔ ዓላማ የነበረው ለሕዝቡ በቤተሰብ ውስጥ ሃላፊነታቸውንና ግዴታቸውን እንዲያውቁ የሚገልጥ መጽሐፍን ማዘጋጀት ነው ... ስለዚህም ሙስሊሞች ሁሉ ሃላፊነቶቻቸውን አውቀው ታላቁን አላህን ለማስደሰት በፍፁምነት ያከናውኗቸዋል› 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al-'Elmeyah, 1990, vol. 4, p. 5፡፡
የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡
በንፁህ እስልምና ሴትችን በተመለከተ ከዚህ በላይ የቀረበውም ጽሑፍ እንዳለፉት ተከታታይ ጽሑፎች የሚያሳየን ሴቶች ከወንዶች እጅግ በጣም ዝቅ ተደርገው እንደሚታዩ ነው፡፡
በንፁህ እስልምና መሠረት ሴቶች የተፈጠሩት ለወንዶች የግብረ ስጋ ግንኙነት ደስታን ለመስጠት ብቻ እንጂ እንደ ሰው እንዲታዩም አይደለም፡፡ ሴቶች የግብረ ስጋ ግንኙነትን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ምንም ዓይነት ምክንያት ይኑራቸው፤ በየዕለቱ በወንዶች የሚሰጠው ድጋፍ እንደተፈለገ ሊቀነስ ወይንም ሙሉ ለሙሉ ሊከለከል ይቻላል፡፡ እነዚህ ሁሉ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ በደሎች ምንጫቸው እውነተኛው ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው? ወይንስ ሌላ? የሚሉት ጥያቄዎች አስተዋይ ሙስሊሞችን ሁሉ ሊያጠያይቁ ይገባል፡፡
ለነዚህ ጥቄዎችስ ትክክለኛ መልስን የምናገኘው ከየት ነው? ይህስ እውነት ፈላጊ የሆኑ ሙስሊሞችን አያሳስብምን? ከዚህ በላይ በተከታታይ ከቀረቡት መረጃዎች አኳያ ጥንታዊዎቹም ሆኑ ዘመናዊዎቹ የሙስሊም ሊቃውንት፤ የህግ ዶክተሮች፣ ዑላማዎች፣ ተንታኞችና አስተማሪዎች ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸው አመለካከት አንድ ዓይነት ነው፡፡ እንዲህ ያደረጉት አምነውበት ነው ወይንስ ሃይማኖቱን ለመሸፈን በማለት ነው የሚለው ጥያቄ አሁንም ሊነሳ የሚገባው ቢሆንም መልሱን ለእነሱ እንተወዋለን፡፡ ትንተናቸውም አስተምህሮአቸውም ከተናገሩት ማስረጃዎች ጋር በሚገባ ጋር ስለተገለጠ ከእነርሱ ትክክለኛና አሳማኝ መልስ ሊገኝ አይችልም፡፡ ታዲያ እውነተኛ መልስ ከየት ነው የሚገኘው? ለነዚህ ጥያቄዎች መልሱ የሚገኘው የፍጥረት እና የሰው ልጆች ፈጣሪ እውነተኛው እግዚአብሔር ቃል ውስጥ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በወጥነት ማለትም ያለምንም መምታታት የሚገልጠው፡ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች፤ በአጠቃላይ ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር እኩል እንደተፈጠሩ፣ በሴቶችና በወንዶች መካከል በፆታ፣ በዕድሜ እና በጎሳ የተነሳ የተሰጠ ወይንም የተጠቆመ ምንም ልዩነት እንደሌለ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ወንዶች ሴቶችን እንደራሳቸው መውደድ እና ማክበር አለባቸው፡፡ በተለይም በጋብቻ ውስጥ ያሉት ወንድና ሴት እርስ በእርስ መከባበርን፤ እርስ በእርስ መዋደድን እኩል ማሳየት እንዳለባቸው ታዘዋል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት የሚናገረው ወንዶች ሚስቶቻቸውን ማክበር እንዳለባቸው ነው፡፡ አማኝ የሆኑ ወንዶች ሚስቶቻቸውን እንዲያከብሩ ሲታዘዙ የተነገራቸው ነገር ‹አብረዋቸው መንግስተ ሰማይን ስለሚወርሱ› እንደሆነም በግልጥ ተጽፏል፡፡
ከዚህም ባሻገር የእውነተኛው ፈጣሪ የእግዚአብሔር ቃል የሚናገረው ወንዶችም ሆኑ ሴቶች እኩል ኃጢአተኞች መሆናቸውን ነው፡፡ በፆታ ምክንያት እግዚአብሔር ምንም ልዩነትን ስለማያደርግ ሁለቱም በእግዚአብሔርም ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት የሚችሉት በአንድ መንገድ ብቻ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ አንዱም ብቸኛ መንገድ ለእያንዳንዳችን ኃጢአት መስዋዕት ሆኖ ስለ እኛ በመስቀል ላይ በተቀጣው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ወደ ቅዱስ እግዚአብሔር መቅረብ ብቻ እንደሆነ ያሳያል፡፡
አንባቢዎች ሆይ! ወደእውነተኛው ፈጣሪ እግዚአብሔር እንድትቀርቡና ከዘላለም ፍርድ ሰዎችን ለማዳን እራሱ ባዘጋጀላችሁ መንገድ እንድትመጡ፣ በፊቱ ከኃጢአታችሁ ንስሐ እንድትገቡ ስለ ጌታ ኢየሱስም ሲል ምህረትና ይቅርታን እንዲሰጣችሁ እንድትጠይቁት ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን፡፡ ጌታ እግዚአብሔር ይርዳችሁ አሜን፡፡
ወደ ክፍል አስር ይቀጥሉ::
የትርጉም ምንጭ: The Place of Women in Pure Islam
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ